Quantcast
Channel: DW Amharic

በኢትዮጵያ አሳሳቢው የተፈናቃዮች ይዞታ ተስፋና መፍትሄው

የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል የተባለው ድርጅት በዓመታዊ ዘገባው በዓለም ላይ የተዘነጋ የመፈናቀል ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ ካላቸው መካከል ኢትዮጵያን ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። በግጭቶችም ይሁን በሌሎች ተፈጥሮአዊ አደጋዎች በኢትዮጵያ ከመኖሪያቸው ከተፈናቀሉ ሰዎች መካከል የምግብ አቅርቦት እንደተቋረጠባቸው በምሬት...

View Article


መጪው ምርጫና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ይዞታ

ኢትዮጵያ 7ተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ የ11 ወራት ቀርቷታል። ሀገሪቱ ከላይ ከላይ ስትታይ በበርካታ ዘርፈ ብዙ ፕሪጀክቶች ክንውን ተጠምዳለች። በአንጻሩ ከአንድ አካባቢ ወደሌላው ለመጓጓዝ በአየር ካልሆነ በምድር እንደማይሞከር የሚናገሩ በርካቶች ናቸው። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስለቀጣዩ ምርጫ የሚያደርጉት ዝግጅት ግን...

View Article


እንወያይ፤ «የሕዝብ ለሕዝብ» የተባለለት ግንኙነት ወዴት ያመራል?

በሕዝብ ለሕዝብ ስም እንዲህ አይነት ግንኙነቶች መጀመሩን ብዙዎች እየተቹት ይገኛሉ። በሌላ ወገን ደግሞ ግንኙነቱ መጀመሩን ያለፈ ቁስልን በማሻር ወደፊት የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር በር ከፋች እንደሆነ የሚገልጹም አሉ።

View Article

የሊቨርፑል እና የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ቁልፍ ተጫዋች የነበረው ዲዬጎ ዮታ እና ወንድሙ አንድሬ ሲልቫ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የሊቨርፑል እና የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ቁልፍ ተጨዋች የነበረው ዲዬጎ ዮታ እና የወንድሙ አንድሬ ሲልቫ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ። በመኪና አደጋ ባለፈው ሐሙስ ሕይወታቸውን ያጡት ወንድማማቾች ሥርዓተ-ቀብር የተፈጸመው በፖርቹጋል ምሥራቃዊ ፖርቶ በምትገኘው ጎንዶማር የተባለች ከተማ ውስጥ ነው።

View Article

የአውሮፓ ኅብረት የተመ ሰብአዊ መብቶች ምክር ቤትን ተጠቅሞ ጥቃት እንደሚፈጽምባት ኤርትራ ከሰሰች

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል የአውሮፓ ኅብረት ሀገራቸውን ለመቅጣት የተ.መ. የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤትን እንደ መሣሪያ እንደሚጠቀም ከሰሱ። የማነ ኅብረቱን የወነጀሉት መንግሥታቸው በኤርትራ ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ለመመርመር የሚሾሙ ባለሙያ ሥልጣን እንዲያበቃ ያቀረበው ጥያቄ...

View Article


ብዙዎችን ያስጨነቀው የሙቀት ማዕበል

የሰሜኑ ንፍቀ ክበብ የበጋ ወራት በይፋ ከጀመረ አንስቶ በርካታ ሃገራት ለቀናት የዘለቀ ኃይለኛ ሙቀት እያስተናገዱ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ፤ በአሁኑ ጊዜ ምድር በሁሉም ቦታ እጅግ ሞቃትና ለሁሉም በጣም አደገኛ እየሆነች ነው በማለት ሁኔታውን ገልጸዋል።

View Article

የ"ብሩህ ትውልድ"የልዩ ክህሎት ሥልጠና በኢትዮጵያ

በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በ28 ማዕከላት ከ800 በላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የክረምት ልዩ የክህሎት ስልጠና ለመስጠት መዘጋጀቱን ብሩህ ትውልድ ድርጅት አስታወቀ። የብሩህ ትውልድ በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች ለሃገራቸው መሰረታዊ ችግሮች መፍትሄ የሚያፈላልጉና ዐዲስ ነገር መፍጠር የሚችሉ ዜጎችን ማፍራት ያስቻለ...

View Article

ትኩረት በአፍሪቃ፤ የናይጄሪያ የምርጫ ዝግጅት፤ የሩዋንዳና የኮንጎ ስምምነት

ይህ በታጣቂዎች ላይ ቅሬታን ፈጥሯል ያሉት የፖለቲካ ተንታኙ ይህም የስምምነቱን ተፈጻሚነት አደጋ ላይ እንደሚጥለው ተናግሯል። የኮንጎ መንግሥት በበኩሉ እነዚህ የ ኤም አይ 23 ሚሊሺያዎች ድርጊት በማውገዝ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው አጥብቆ አሳስቧል።

View Article


“በትግራይ በኩል ምንም ዓይነት የጦርነት ፍላጎትም ሆነ ዝግጅት የለም” – ህወሓት

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ “በትግራይ በኩል ምንም ዓይነት የጦርነት ፍላጎትም ሆነ ዝግጅት” እንደሌለ አስታወቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላቀረቡት ማብራሪያ በሰጠው ምላሽ ህወሓት በኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት ላይ ብርቱ ውንጀላ አቅርቧል። ዐቢይ በምክር ቤቱ ውጊያ “ከተጀመረ ነገር...

View Article


የቤንዚን እጦት ፈተና የሆነባቸው የሀዋሳ ከተማ አሽከርካሪዎች

ሀዋሳ በህጋዊ ማደያዎች ነዳጅ ማግኘት ሲበዛ አዳጋች ነው፡፡ በከተማው የነዳጅ አቅርቦት የለም ፡፡ በጥቁር ገበያው ላይ ግን አቅርቦቱ ተትረፍርፎ በየጎዳናው በፕላስቲክ ኮዳዎች ይቸበቸባል፡፡ ዋጋው ግን የሚቀመስ አይደለም ፡፡ መንግሥት በማደያዎች በሊትር 90 ብር እንዲሸጥ ብሎ ካስቀመጠው እዚህ በሁለትና በሦስት እጥፍ...

View Article

የነዳጅ እጥረት ሥራ ማስተጓጎሉ

በመንግሥት ድጎማ የሚገባን የነዳጅ ዘይት መሰወርና ወደ ጎረቤት አገሮች በሕገወጥ መንገድ መላክ ለነዳጅ ዘይት አቅርቦት እጥረት ምክንያት መሆኑ ተገለፀ። እንደ አዲስ የተከሰተዉ የነዳጅ እጥረት በአማራ ክልል ደቡብና ሰሜን ወሎ ተሽከርካሪዎችን ለቀናት በነዳጅ ማደያ እንዲቆሙ እያደረገ ነው።

View Article

በኢትዮጵያ ፈታኝ ሆኖ የቀጠለው የነዳጅ አቅርቦትና መዘዙ

ኢትዮጵያ ውስጥ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ጨምሮ አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት በብርቱ መፈተናቸውን እየገለጹ ነው። ማደያዎች ነዳጅን በሕገወጥ እያወጡ ዋጋን ጨምረው መሸጥና ወር እየተገባደደ በመጣ ቁጥር ጭማሪ ይደረጋል በሚል ምርቱን መደበቅ መዘዝ እያስከተለ ነው ተብሏል።

View Article

ሪዮ ዲ ጄኒሮ፤ የብሪክስ አባል ሃገራት የመሪዎች ጉባኤ ሪዮ ዲ ጄኒሮ ብራዚል ውስጥ ዛሬ ተጀመረ

ጉባኤው ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠንካራ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ምላሽ መስጠትን ጨምሮ በዋና ዋና የጥምረቱ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

View Article


ዉይይት፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ የነዳጅ ዘይት ዋጋ መናር፣እጥረትና እስከፊ ጫናዉ

ነዳጅ ዘይት ከመወደዱ በተጨማሪ በየነዳጅ ማደያዉ አለመገኘቱ ወይም እጥረቱ ለብዙዎች ፈተና ሆኗል።የኢትዮጵያ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ እንዳሉት ከዉጪ የሚገባዉ የነዳጅ መጠን አልቀነሰም።ባለሥልጣናቱ ለእጥረቱ «ስግብግብ» እና «ኮንትሮባንድ» ነጋዴዎች ያሏቸዉን ወገኖች ተጠያቂ ያደርጋሉ

View Article