ፖሊስ በቤተክርስቲያኗ ላይ የተካሄደውን የመሬት ወረራን ባለመከላከል ለተከሰተው ችግርም ፈጥኖ መፍትሄ ባለመስጠት ቅሬታ ቀርቦበታል።የድሬዳዋ ፖሊስም በወቅቱ ህግን ለማስከበር በሚፈለገው መጠን አለመሰራቱን ለDW አስታውቋል።የድሬዳዋ አስተዳደር በበኩሉ ከመሬት ወረራው እና ህገ ወጥ ከሚባሉ ግንባታዎች ጋር ለተያያዙ ችግሮች መፍትሄ አስቀምጫለሁ ይላል።
↧
የድሬዳዋው የመሬት ወረራ ፣አስተዳደሩ እና ፖሊስ
↧
በሞዛምቢክ እና ዚምባብዌ የበረታው የኢዳ ማዕበል
ኢዳ በተባለው ኃይለኛ ማዕበል በተመታችው ሞዛምቢክ የሞቱ ሰዎች 417 ደርሰዋል። በዚምባዌ ሌሎች 259 ሰዎች ሲገደሉ 300 ገደማ የገቡበት አይታወቅም። በሰዓት 200 ኪ.ሜ. የነጎደው የኢዳ አውሎ ንፋስ ተራራ እየናደ መኖሪያ ቤቶች ቀብሯል። ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት ወድመዋል። ከአደጋው የተረፉ ኮሌራን ለመሰሉ ተላላፊ በሽታዎች ተጋልጠዋል።
↧
↧
የዶይቼ ቬለ አመራሮች ጉብኝት በጎንደር
የDW ከፍተኛ አመራሮች ልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ ጉብኝት አድርገዋል። ከልዑካኑ መካከል የDW ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፒተር ሉምቡርግ፣ የአፍሪካ ክፍል ተጠሪ ክላውስ ሽቴከር እና የአማርኛዉ ክፍል ተጠሪ ሉድገር ሻዶምስኪ ይገኙበታል።
↧
ዉይይት:-ሥጋትና ተስፋ ያጠላበት የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ለዉጥ
መንግሥት ሃገሪቱን «ለዉጡን» ከየት ተነስቶ የት መድረስ እንደሚፈልግ ፍኖተ ካርታ አስቀምጦ ለሕዝብ ግልፅ መደረግ አለበት። ከኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ምን ይጠበቃል? ምን ማድረግ ነዉ የምንፈልገዉ የሚለዉ ለሕዝብ በግልፅ ይቀመጥ። ለዉጡ የተገነባዉ አሸዋ ላይ ሳይሆን ኮንክሪት ላይ ነዉ። ለዉጡን መቀልበስ አይቻልም» ተወያዮች የሰነዘሩት ኃሳብ
↧
መዝናኛ፦ ከገረመው ደንቦባ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች የተሳተፈችው በጎርጎሮሳዊው 1956 ዓ.ም. በሜልበርን ነበር። የልዑካን ቡድኑ ከሰባት ቀናት ጉዞ በኋላ አውስትራሊያ ሲደርሱ ተዳክመው ነበር። ገረመው ደንቦባ "ሰባት ቀን አየር ላይ ስንቆይ ምግብ የለ ደርቀን ሥጋ እና አጥንታችን ተጣብቆ ከጦር ምርኮኝነት የተለቀቅን ይመስል ነበር"ሲሉ ያስታውሱታል።
↧
↧
በፈረንሳይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለጌዲዮ ተፈናቃዮች ርዳታ
ባሳለፍነው ቅዳሜ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማሕበር ፓሪስ ላይ ተፈናቅለው ለረሃብ እና ችግር ለተጋለጡ የጌዲዮ ተወላጆች የርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄደ። የጌዲዮ ሕዝብ መፈናቀል ብሎም በጊዜው በቂ ትኩረት እና ርዳታ አለማግኘቱን ተከትሎ ለከፋ ረሃብ እና እንግልት መዳረጉ የሰሞኑ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል።
↧
ኢትዮጵያ፣ የግጭትና ዉዝግብ ምድር
የጎሳ ግጭቱ አጎዞ አጎዞ ርዕሠ-ከተማ አዲስ አበባ «የኔነች-አይደለችም» እሰጥ አገባ ቀስቅሷል።በአዉሮፕላን አደጋ ምክንያት ላጭር ጊዜ ተዳፎኖ የነበረዉ የአዲስ አበባ ጉዳይ ከከተማይቱ-ባለስልጣናት እስከ ጋዜጠኞች፣ ከጠቅላይ ሚንስትሩ፣ እስከ ፖለቲካ አቀንቃኞች ያሉትን ተራበተራ ከዉዝግብ ሞጅሯል።
↧
የ«DW» ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ
ከፍተኛ አመራሮች ያካተተው የ «DW» ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ኹኔታ ላይ ከመገናኛ ብዙኃን እና የሲቪክ ማኅበራት መሪዎች ጋር ተወያዩ። ውይይቱ የተዘጋጀዉ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ቫግነር ነው።
↧
የዱልሚ ዲድ ንቅናቄ መሥራቾች በጅግጅጋ ታሰሩ
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ-መሥተዳድር ሙስጠፋ ዑመር ከሥልጣናቸው ሊለቁ ይገባል የሚል ጥያቄ አቅርበዋል የተባሉ የዱልሚ ዲድ ንቅናቄ መሥራቾች በጅግጅጋ ታሰሩ። በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ኸድር ጅግሬና አቶ አብዲ ኑር ናቸው። የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አማካሪ ሁለቱ ግለሰቦች መታሰራቸውን አረጋግጠዋል።
↧
↧
ከ700 በላይ አርጎባዎች ከመተሐራ ከተማ ተፈናቀሉ ተባለ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ወረዳ እና በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ከ700 በላይ አርጎባዎች ከመተሐራ ከተማ ተፈናቅለዋል ተባለ። በመተሐራ ከተማ ደርሶብናል ባሉት ማስፈራሪያ የሸሹ ሰዎች በአዋሽ ከተማ መጠለያ ይገኛሉ።
↧
የመጋቢት 16፣2011 የስፖርት ዝግጅት
ከሁለት አመት የወሊድ እረፍት በኋላ ወደ ውድድር የተመለሰችው ኬንያዊት አትሌት ፕሪስካ ጂፕቶ 1፡08፡26 በመግባት ቀዳሚ ስትሆን ፥መሰረት መልካ 1፡10፡39 ሰከንድ በመጨረስ ሁለተኛ ሆናለች ሌላዋ ኪንያዊት አትሊት ሙርጊ ዋመቡኢ ደግሞ ሶስተኛ ሆናለች።
↧
የመጋቢት 16፣2019 የስፖርት ዝግጅት
በዴንማርክ ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮን ውድድር 582 ታዋቂ አትሊቶች ከ 67 ሀገሮች ተሳታፊ እንደሚ ሆኑ የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፊዲሪሽን ትናንት አስታውቀዋል። በዚህ ውድድር 14 ኢትዮጵያውያን ወንድ እና 14 ሴት አትሊቶች በአዋቂና በ ከ20 አመት በታች በሚደረገው ውድድር ተሳታፊ እንደሚሆኑ የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፊዲሪሽን አስታውቋል።
↧
በኢትዮጵያ የተደጋገመው የደን ቃጠሎ
ካለፈው ሐሙስ ዕለት ጀምሮ በባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል። እስካሁን በሁለት አካባቢዎች ከተነሳው እሳት አንዱን በአካባቢው ኅብረተሰብ እና የፀጥታ ኃይሎች ርብርብ ማጥፋት የተቻለ ሲሆን አንደኛው ገና አልጠፋም። ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የደን ቃጠሎ መደጋገሙን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ይናገራሉ።
↧
↧
ሕገ ወጥ ግንባታና የመሪት ወረራ በድሪደዋ
ፕላንን መሰረት ባደረግ ዘመናዊ አመሰራረቷ ትታወቅ ለነበረችው ድሬደዋ የታሪክ ምስክር ሆነው ከቆዩት ነባር መንደሮቿ ውጭ ያሉት መዳረሻዎች በሙሉ ያንን የቀደመ አሻራ አይገልፁም ፡፡ አስተዳደሩ ዛሬም ይሄን እያለ ባለበት በዚህ ጊዜ በአንድ ቀን ዕድሜ ያውም ምሽቱን ብቻ በመጠቀም ተሰርተው የሚያድሩ ግንባታዎች ቁጥር በርካታ ነው ፡፡
↧
108ኛው ፓርቲ ተመሠረተ
በኢትዮጵያ 108 ኛ ሆኖ የተመሠረተው ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ተንሰራፍቶ የቆየውን አግላይ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከስረ መሠረቱ ለማስወገድ እሠራለሁ አለ።
↧
ብሬግዚት ያስከተለው ፍልሰት
ብሪታንያ ከአውሮጳ ህብረት አባልነት ለመውጣት የተስማማችበት የብሬግዚት ውል የብሪታንያ ፖለቲከኞችን ማወዛገቡ ቀጥሏል። በሌላ በኩል ብሪታንያ ከህብረቱ እንድትወጣ ከሚጠይቀው ከዛሬ ሁለት ዓመት ተኩሉ የህዝበ ውሳኔ ውጤት በኋላ በርካታ ብሪታንያውያን ወደ ሌሎች ሀገራት እየፈለሱ ነው። ከመካከላቸው ደግሞ አየርላንድ የብዙዎቹ ምርጫ ናት።
↧
ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ የዐባይ ወንዝ ዉዝጋባቸዉን ይፍቱ ተባለ
በኢትዮጵያ የሕዳሴዉ ግድብ ግንባታ መጀመርን ተከትሎ ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ በናይል ወንዝ ላይ የገቡበትን ዉዝግብ ሊፈቱ የሚገባ መሆኑን « ክራይሲስ ግሩፕ» የተባለዉ በግጭቶች ላይ የሚሰራዉ ድርጅት በቅርቡ ይፋ ያደረገዉ ዘገባ አስታዉቋል።
↧
↧
የአጼ ቴዎድሮስ ቆንዳላ መመለስ ታሪካዊ ነዉ
ባለፈዉ ሳምንት ብሪታንያ ከዛሬ 150 ዓመት በፊት ከንጉሠ-ነገሥት ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ አስከሬን ላይ ቆርጣ የወሰደችውን የሹሩባ ቁራጭ መመለስዋ ኢትዮጵያዉያን አስደስቶአል፤ ስለ ቅርስ ጉዳይ የሚቆረቆሩ ምሁራንንም እሰየዉ አስኝቶአል። የታሪክ አዋቂዉ አቶ አሉላ ፓንክረስት የአጼ ቴዎድሮስ ቁንዳላ መመለስ ታሪካዊ ነዉ ፤ ሲሊ ነዉ የገለፁት።
↧
DW የለውጥ ሂደቱ ተጓዳኝ
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የጀመሩት የማሻሻያ አንድ ዓመት ከሆነው በኋላ DW ኢትዮጵያ ውስጥ እንቅስቃሴውን ይበልጥ በማስፋፋት ላይ ነው። የDW ዳይሬክተር መቶ ሚሊየን ሕዝብ ባለባት የምሥራቅ አፍሪቃዊቷ ስልታዊ ጠቃሚ ሀገር ኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ባካሄዱትበት ወቅት የተለያዩ የራዲዮ እና የኢንተርኔት ተጓዳኝነት ውሎችን ተፈራርመዋል።
↧
የDW ወኪሎች ሥልጠና
የDW ሥራ አስፈፃሚ ፔተር ሊምቡርግ የመሩት የጣቢያዉ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ኢትዮጵያ ከሚገኙ የDW ዘጋቢዎች ጋርም ተወያይቷልአዳዲስ ለተቀጠሩ ለDW በተለይም ለአማርኛዉ ክፍል ዘጋቢዎች ለሥራቸዉ የሚያስፈልጓቸዉ አዳዲስ መሳሪያዎችን አስረክቧልም
↧